እደግመዋለሁ የሀጎስ ጌታነት የቶላ ዘበኝነት ሊያበቃለት ይገባል

0
373

እደግመዋለሁ የሀጎስ ጌታነት የቶላ ዘበኝነት ሊያበቃለት ይገባል። ይህ ዘረኝነት አይደለም የጸረ ዘረኛ ስርዓት አቋም እንጂ። ዘረኝነት ( racism ) ትርጉሙ ምንድነው? ዘረኘት ማለት አንድ ግለሰብ ወይንም ቡድን በሌላው ላይ ያለውን የ ጥላቻ /ንቀት አመለካከት በተቆጣጠረው ስልጣን ተጠቅሞ ሲጎዳ ነው (Racism is Prejudice plus power)። በዚህ ትርጉም ተመስርተን ዛሬ እትዮጲያ ውስጥ ባለው ተጨባጭ ሁኔት ዘረኛ መሆን የሚችለው ስልጣን ላይ ያለው ቡድን ብቻ ነው። ሌሎች የ ጥላቻ (hate)፣ ንቃት ወዘት አመለካከት ሊኖራቸው ይችላል። ያንን አመልካከታቸውን በተጨባጭ ስራ ላይ ለማዋል የፖሊቲካ ስልጣን እስከሌላቸው ድረስ ዘረኛ ( racist) መሆን አይችሉም።
የትግሬ ገዢ ቡድን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የኦሮሞን ገበሬዎች እያፈናቀለ እራሱን እና የራሱን ቡድን ማደላደል የለበትም የሚለው አቋም የሚያስከፍችሁ ከሆነ፤ አሁንም ደግመዋለሁ። በቶላ አንጡራ ሀብት ምሬት ላይ ሀጎስ ኢንቨስተር፣ ቶላ አሽከር እንዲሆን አይፈቀድም፤ ያንን እያስፈጸመ ያለው ዘረኛ ስርዓትም ሊወገዝ፣ ሊደመሰስ ይገባዋል!!
የዛሬዋ እትዮጲያ በትግሬ ገዢ ቡድን መዳፍ ስር መሆኗን ከዳችሁ ማሳመን ለምትፈልጉት ሂዱና መጀምሪያ የራሳችሁን ህሊና ሳምኑ።

By Jawar Mohammed

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here