በጅማ ዩኒቨርሲቲ የእጅ ቦምብ ተወረወረ | 33 ተማሪዎች ተጎድተዋል | 2 ተማሪዎች በሞት አፋፍ ላይ ናቸው

0
535
Jima University

Jima University(ዘ-ሐበሻ) ትናንት ማምሻውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ባለበት ወቅት በተወረወረ የእጅ ቦምብ በ33 ተማሪዎች ላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰ ተዘገበ::

የ እጅ ቦምቡን ወደ ተማሪዎቹ ላይ ማን እንደወረወረው ባይገለጽም ከሕወሃት ወታደሮች ና ቅጥረኞች ውጭ የሚያደርገው እንደሌለ ተማሪዎች በመግለጽ ላይ ናቸው:: በትናንቱ የ እጅ ቦምብ አደጋ በ33ቱም ተማሪዎች ላይ በተለያዩ የሰውነታቸው አካል ክፍል ላይ ጉዳት መድረሱን ያስታወቁት እነዚሁ የዜና ምንጮች ሁለቱ ወጣት ተማሪዎች ግን ሕይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ላይ እንዳለ ገልጸዋል::

የኦሮሞ ተማሪዎች ሰላማዊ ጥያቄ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በሁለት አሃዝ የሚቆጠሩ ወጣቶች በስ ር ዓቱ መገደላቸው የሚታወስ ነው:: በተጨማሪም ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተቃውሞ ካለማቋረጥ ከሚሰማባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ ነው::

ዘ-ሐበሻ በዚህ ተማሪዎች ላይ በተወረወረውና ለ33 ተማሪዎች አካል መጎዳት ምክንያት ስለሆነው የ እጅ ቦምብ አደጋ ተጨማሪ መረጃዎችን እያሰባሰበች ነው::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here