የደህንነት ኃይሎች በአዳማ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ያወደመውን የእሳት አደጋ ከተቃዋሚዎች ጋር ለማያያዝ እየሰሩ መሆኑ ተጋለጠ

0
326

Adama Fire

(ዘ-ሐበሻ) ከትናንት በስቲያ በአዳማ ከተማ ቀበሌ 10 (ፖስታ ቤትና በከልቻ) በሚባለው አካባቢ ስድስት የመኖሪያ ቤቶች፣ አንድ ሱቅና አንድ የከባድ ጭነት መኪና ተሳቢ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ተከትሎ ስርዓቱ አደጋውን ከተቃዋሚዎ ጋር ለማያያዝ እየሞከረ መሆኑ ተሰማ::

ፖሊስ አደጋው በደረሰበት ወቅት የአደጋውን መን ስኤ እያጣራሁ ነው በሚል ይህን ጉዳይ አድበስብሶት ካለፈ በኋላ የደህንነት ኃይሎች ቃጠሎው የደረሰበት አካባቢ በመሄድ ቭዲዮዎችን በመቅረጽ እንዲሁም የተጎዱትን ሰዎችም ለማነጋገርና አደጋው የደረሰው በተቃዋሚ ሃይሎች በንጹሃን ንብረት ላይ የተወሰደ ለማስባል እየሰሩ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አጋልጠዋል::

የደህንነት ኃይሎች የራሳቸውን ሰዎች በማዘጋጀት ንብረቱ በቃጠሎ የደረሰበት ቦታን ከጀርባ እያሳዩ ሰዎችን ቃለምልልስ እያደረጉ ሲቀርጹ መታየታቸውንም ምንጮች አጋልጠዋል::

በተለይ የኦሮሞ ተማሪዎች ሰላማዊ ጥያቄ በተለያዩ ከተሞች መቀጠሉን ተያይዞ ሕወሓት የሚመራው መንግስት ይህን ሰላማዊ ጥያቄን ከሃገርና የንጹሃንን ንብረት ከማፈራረስ ጋር በማያያዝ ለማቅረብ እየተጋ ባለበት በዚህ ወቅት እንዲህ ያሉ አደጋዎች መፈጠራቸው የሚያስገርም አይደለም የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች 4 ሚሊዮን ብር የወደመበትን ይህን አደጋ ከፖለቲካ ጋር ለማያያዝ መሞከሩ ግን ያሳፍራል ብለዋል::

በዚሁ በአዳማ ከተማ በደረሰው የ እሳት ቃጠሎ 2 ሰዎች መጎዳታቸውን መንግስታዊ ሚድያዎች መዘገባቸው አይዘነጋም::

በአደጋው የሰው ህይወት አለማለፉንና የቃጠሎው መንስኤም እየተጣራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here