AKEEKKACHIISA:
Fincila Oromoota naannawa Shaashamannee kana kararraa maqsuuf jecha Wayyaaneen tooftaa amantiifi sabaaf sablammoota walitti buusuu fayyadamuuf kaatee jirti. Kanaafuu shira kana fashalsuuf ummanni keenya dhaabbilee amantii hunda tiksuu, tarkaanfilee gurmuulee amntii muufachiisu danda’an irraa of qusachuu, akkasumas sabaaf sabalammoota naannawa san jiran walin walitti akka hin buune of eeggannoo cimaa barbaachisa, Kanarratti qeerroon, manguddoon, haawwan, hogganoonni amantifi hojjattoonni mootummaa shoora isinirraa eeggamu akka baatan abdii qabna.
ማሳሰቢያ:
ትላንትና እንደተገለፀው የወያኔ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ የተያያዘውን ትግል ስም ለማጥቆር ሲል በብሄሮች መካከል የሃይማኖት ግጭት ያለ ኣስመስሎ ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ነው። ህዝባችን ይህንን ተገንዝቦ የስርኣቱ ቅጥረኞች በህዝብ ተመስለው የጥፋት ተልእኮኣቸውን እንዳይፈፅሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል። በዚህም መልኩ፣
1. ሁሉም የሃይማኖት ተቁዋማት ጥብቅ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል። ይህንን ለማሳካት የተለያዩ ሃይማኖት ተከተይ የሆናችሁ ታጋዮቻችን መረጃን በንቃት በመቀባበል በመስጊዶችና በኣብያተ-ክርስቲያኖች እንዲሁም በመቃብር ስፍራዎች ላይ ምንም ኣይነት ጥቃት በጥፋት መልእክተኞቹ እንዳይደርስ መጠበቅ።
2. ኦሮምያ ውስጥም ሆነ በኣጎራባች ኣካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ማናቸውም ብሄር ብሄረሰቦች መነካት የለባቸውም። በሚስተጋቡት መፈክሮች መካከል ምንም ኣይነት ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችን ማስቀየም የሚችሉ ቃላቶች መጠቀም ተገቢ ኣይደለም። ሰላማዊ ሰልፍ በሚካሄድበት ወቅት በተቻለ መጠን የሌሎች ብሄር ብሄረሰብ ተወላጆች በሚበዙባቸው ቀበሌዎች ውስጥ ባይሆን ይመረጣል። ይህም የስርኣቱ የጥፋት መልኣክተኞች ግጭት ለመጫር የሚረዳቸውን ኣጋጣሚ ይቀንሰዋል።
3. የግል ንብረቶች ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባቸዋል እንጂ የጥቃት ኢላማ መሆን የለባቸውም። የኦሮሞም ሆነ የማንኛውም ብሄር ተወላጅ የግል ንብረት መነካት ኣይኖርበትም። ሾልከው እየገቡ ወጣቶቻችንን ለማሳሳት የሚፈልጉ ጠብ-ኣጫሪ የጠላት ተላላኪዎችን ኣንቅስቃሴ በንቃት መከታተልና የጥፋት ኣላማቸውን ማክሸፍ ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት።
4. ማህበራዊ ኣገልግሎት ሰጪ የሆኑት የመንግስት ተቁዋማት እንዳይነኩ መጠንቀቅ ያሻል። ከነዚህም መካከል የጤና ተቁዋማት፣ ኣምቡላንሶች፣ ትምህርት ቤቶች ወዘተ ዛሬም ሆነ ነገ ህዝብን ስለሚያገለግሉ በንቃት ሊጠበቁ ይገባል።