Announcement: Oromiawide protests this Saturday/ መግለጫ፡ መጪው ቅዳሜ ለት በመላው ኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳ

0
565

By: Jawar Mohammed

በትናንትናው እለት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በአስርታት ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ወያኔን ተቃውሞ በሰላም ወደ ቤቱ ተመለሰ። በጣም ጥሩና ታሪካዊ ሰልፍ ነበር። በእለቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋል ግን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ አወዳይ ከተማ ወጣቶች ሰልፍ ወጥተው በአጋዚ አልሞ ተኳሾች 26ቱ ቆስለው እስከ አሁን 6 ሞተዋል። ይሄንን እንደምሳሌ ጠቀስኩ እንጂ ኦሮሚያ ውስጥ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት እሩምታ ሲፈጅ አዲስ አይደላም። ባለፉት 9 ወራት ካ600 በላይ ዜጎች ተገድለዋል፣ 5000 የሚሆኑ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸውል። ይሄንን ቁጥር ወስደን ብናሰላው፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በየእለቱ ባማካይ ከሁለት እስከ ሶስት ሰዎች ኦሮሚያ ውስጥ በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሲገደሉ እንደነበረ ማየት ይቻላል። ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም የአምባገኖች ጸባይ ነው ተብሎ ሲታለፍ ነበር። ነገር ግን ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ የሚገደልው የኦሮሚያ ህዝብ ብቻ መሆኑ ግልጽ እየሆነ ሲመጣ ነገሮችን መለሰን እንድናጤን አድርጎናል።

ለመሆኑ በተለያዩ ክልሎች ለወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች የተለያየ ምላሽ ምክንያቱ ምንድ ነው?
1) የኦሮሚያ ሰልፈኞች የጦር መሳሪያ ይዘው አለምውጣታቸው። ምክንያቱም እንደሚታወቀው ባለፉት 25 አመታት ተደጋጋሚ ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ በኦሮሚያ ሲካሄድ ነበር። እናም በግልጽ የታጠቀው ህዝብ አናሳ ነው። በተጨማሪም የኦሮሞ አመራሮች ህዝቡ መሳሪያ ይዞ እንዳይወጣ ሲማጸኑ ነበር። ይሄም የተደረገበት ምክንያት ያቺ ሀገር እና ህዝብ ወደ ዳግም ጦርነት ሳይገቡ በነፍጥ-አልባ ትግል ለውጥ ለማምጣት ካለ ምኞት የተነሳ ነው። ነገር ግን ይህን የኦሮሞን ሰላም ወዳድነት ህወሀቶች እንደ ፈሪነት መቁጠራቸው ገሃድ ወጥቷል።

2) ባለፉት 9 ወራት በኦሮሚያ ውስጥ በተካሄደው ትግል ብዙ ከተሞች ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሲወጡ እንኳን የትግሬዎች ንብረት እና ህይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል። ይህ አቋም ግን ሀወሀቶች እንደ ጅልነት (naivity and harmlessness) የተቆጠረ ይመስላል።
ባጠቃልይ የህወሀት መሪዎች እንድን ህዝብ የሚሰሙት በጠመንጃ ሲጋፈጣቸው እና ዘመዶቻቸው ሲነካ ብቻ መሆኑን ደጋግመው አረጋግጠዋል። ለኦሮሞ ህዝባ ያላቸውን መጠን ያለፈ ንቀት እና ጥላቻ በተደጋጋሚ አሳይተዋል። እናም አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨ ስልማይችል የኦሮሞ ህዝብ እራሱን ከተከፈተበት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመታገድ የስትራቴጂ ለውጥ ሊያደርግ እየተገደደ ነው። ሆኖም ግን ወደዚህ ዓይነቱ መመለሻ የሌለው መንገድ ከመግባታችን በፊት የመጨረሻ እንድል መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁም መሰረት የሚቀጥሉት እርምጃዎች ይወሰዳሉ:

1. በመጪው ቅዳሜ በኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጁ ሰልፎች ይካሄዳሉ። እነዚህ ሰልፎች ልክ እንደ ከዚህ በፊቶቹ ሁሉ ፍጹም ሰላማዊ ይሆናሉ። በሰላማዊ ሰልፎቹ ላይ መንግስት ኦሮሞ ላይ እያካሄደ ያለውን ግድያ ባስቸኳይ እንዲያቆም፣ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ካላንዳች ቅድመ ሁናቴ እንዲፈቱ፣ ኦሮሚያን በኣጋዚ ጦር ማስተዳደር እንዲቆም፣ ህዝቡ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ እንዲጠበቅ የሚሉና የመሳሰሉ ሌሎች መሰረታዊ መብቶችን መከበር የሚጠይቁ ጥያቄዎችና መፈክሮች እንዲንጸባረቁ ይደረጋል።

2. ለዚህ ሰልፍ ፍቃድ አይጠየቅም። በህጉ መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የሚያስፈልገው መንግስትን ማሳወቅ ብቻ በቂ ነው። ይህ ጽሁፍ እንደማስታወቂ እንዲረዳ ለኦሮሚያ እና ለፌደራሉ መግስት መሰራቤቶች ገቢ አድርገናል። የኦሮሚያም ሆነ የፌደራል የታጠቁ ሀይሎች ሰላማዊ ሰልፎቹን ለማስተጓጎልም ሆነ በእለቱ በህዝቡ ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ ከሆነ ቀጥሎ ለሚመጣው አደጋ ተጠያቂ እንደሚሆኑ በዚሁ ማስጠንቀቅ እንወዳለን። የተቀረው የኢትዮጲያ ህዝብም ለምስክረነት ይህን ግልጽ ማስታወቂያ በጥሞና እንዲያነብልንና ከጎናችንም እንዲሰለፍ ባክብሮት እንጠይቃለን።

‪#‎OromoProtests‬

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here